የዛሬ ምሽቱ የዋልያዎቹ ጨዋታ የቀጥታ የቴሌቪዥን ስርጭት ሽፋን ያገኛል

ዛሬ ምሽት 1 ሰዓት ጂቡቲ እና ኢትዮጵያ ሞሮኮ ላይ የሚያደርጉት የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ የምድብ 4ኛ ጨዋታ በቀጥታ የቴሌቪዥን ሽርጭት ሽፋን ይተላለፋል።

ካናዳ፣ ሜክሲኮ እና አሜሪካ በጋራ በሚያዘጋጁት የ2026 የዓለም ዋንጫ ለማለፍ በአህጉራችን አፍሪካ የማጣሪያ ጨዋታዎች በተለያዩ ምድቦች እየተከናወኑ ሲሆን ሀገራችን ኢትዮጵያን ጨምሮ ግብፅ፣ ቡርኪናፋሶ፣ ጊኒ ቢሳው፣ ጂቡቲ እና ሴራሊዮን የሚገኙበት ምድብ አንድም ዛሬ እና ነገ የምድብ አራተኛ ጨዋታዎችን ያስተናግዳል። ከምድቡ ሦስት ጨዋታዎች መሐከል ደግሞ ወረቀት ላይ ባለሜዳ የነበረችው ነገርግን በሀገሯ ፍቃድ ያለው ስታዲየም የሌላት ጂቡቲ ሀገራችን ኢትዮጵያን በሰሜን አፍሪካዊቷ ሀገር ሞሮኮ የምታስተናግድበት ጨዋታ ይጠቀሳል።

በኤል አብዲ ስታዲየም ምሽት 1 ሰዓት ላይ የሚደረገው የሁለቱ ብሔራዊ ቡድኖች ጨዋታም እንደተለመደው በውድድሩ ባለቤት ፊፋ ድረ-ገፅ በበይነ መረብ በፊፋ+ (Fifa+) የቀጥታ ስርጭት ሽፋን እንደሚያገኝ ተገልጿል።