በሴቶች ፕሪምየር ሊግ ጠንካራ ተፎካካሪ የሆነው መቻል ለቡድኑ አዲስ አሰልጣኝ መቅጠሩ ታውቋል።
ባሳለፍነው የውድድር ዓመት በደረጃ ሰንጠረዡ አራተኛ በመሆን ያጠናቀቀው መቻል የቀድሞ አሰልጣኙ ስለሺ ገመቹን ጋር መለያየቱን ተከትሎ ቡድኑ በምትኩ ወጣቱ አሰልጣኝ መቶ አለቃ አብዱ መሐመድን መሾሙን ክለቡ ለሶከር ኢትዮጵያ አረጋግጧል።
አሰልጣኝ አብዱ መሐመድ ከዚህ ቀድም ለመጀመርያ ጊዜ የተቋቋመውን የሠራዊቱን ቡድን በማሰልጠን ውጤታማ ከሆነ በኋላ ወደ ታዳጊዎች በማምራት ከ17 እና 20 በታች የመቻል ቡድን ያሰለጠነ ሲሆን ከቡድኑ ለፍፃሜ ዋንጫ ማድረሱ ይታወቃል። አሁን ደግሞ የሴቶች ቡድኑን በኃላፊነት እንዲያሰለጠረን መሾሙ ታውቋል።
አስቀድሞ ወደ ዝውውሩ በመግባት ተጫዋቾችን ያስፈረመው መቻል በቀጣይ ጊዚያትም ተጨማሪ ተጫዋቾችን ወደ ቡድኑ የሚቀላቅል የሆናል።