የብሄራዊ ፣ ከ17 እና ከ20 አመት በታች ሊጎች የሚጀመሩበት ቀናት ተራዝመዋል

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ሊግ ፣ ከ17 አመት በታች ፕሪሚየር ሊግ እና ከ20 አመት በታች ፕሪሚየር ሊግ በተለያዩ ምክንያቶች የሚጀመሩበት ቀን ተራዝሟል፡፡

የ2009 የውድድር ዘምነ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ሊግ ተሳታፊ ክለቦች ለዳኞች እና ታዛቢዎች መክፈል የሚገባቸውን ክፍያ እስካሁን መክፈል ባለመቻላቸው የሚጀመርበት ቀን በድጋሚ በ1 ሳምንት ተራዝሟል፡፡ ሊጉ እንዲጀመር የታቀደው ህዳር 17 ቢሆንም በክፍያው መዘግየት ምክንያት ወደ ህዳር 25 ተራዝሞ ነበር፡፡ አሁን ደግሞ እንደገና በ1 ሳምንት ተራዝሞ ታህሳስ 2 እንዲጀመር ተወስኗል፡፡

የኢትዮጵያ ከ17 እና ከ20 አመት በታች ፕሪሚር ሊጎች በእድሜ ምርመራ ችግሮች ምክንያት ወደ ታህሳስ 8 ተሸጋግሯል፡፡ የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ክለቦች ለምርመራ ይዘዋቸው የሚመጧቸው አመዛኞቹ ተጫዋቾች እድሜ ከገደቡ በላይ በመሆኑ ክለቦች ብቁ ተጫዋቾችን እንዲያመጡ በማሰብ ውድድሩ በ2 ሳምንት መራዘሙ ታውቋል፡፡

አብርሃም ገብረማርያም
Follow Me

አብርሃም ገብረማርያም

ይህንን ፅሁፍ ያቀረብኩላችሁ አብርሃም ገብረማርያም ነኝ

ከፎቶው በታች ያለው የፌስቡክ እና ትዊተር ምልክትን ተጭነው ሊያገኙኝ ይችላሉ
አብርሃም ገብረማርያም
Follow Me

አብርሃም ገብረማርያም

ይህንን ፅሁፍ ያቀረብኩላችሁ አብርሃም ገብረማርያም ነኝ ከፎቶው በታች ያለው የፌስቡክ እና ትዊተር ምልክትን ተጭነው ሊያገኙኝ ይችላሉ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *