ኢትዮጵያ ቡና የአስናቀ ሞገስን ኮንትራት ሲያራዝም ፍራኦል መንግስቱን ለድቻ አውሷል

ኢትዮጵያ ቡና የግራ መስመር ተከላካዩ አስናቀ ሞገስን ኮንትራት ለተጨማሪ 3 አመታት አራዝሟል፡፡ ከቡና ወጣት ቡድን በ2007 ወደ ዋናው ቡድን ያደገው አስናቀ በዚህ አመት ኮንትራቱ ይጠናቀቅ ነበር፡፡

አስናቀ ባለፈው የውድድር ዘመን ለባህርዳር ከተማ በውሰት ተሰጥቶ መልካም ጊዜ ካሳለፈ በኋላ ዘንድሮ ወደ ቡና የተመለሰ ሲሆን የአህመድ ረሺድ እና አብዱልከሪም መሀመድን ጉዳት ተከትሎ በሊጉ ጨዋታዎች ላይ ተሰልፎ የመጫወት እድል አግኝቷል፡፡

ከኢትዮጵያ ቡና ጋር በተያያዘ መረጃ አማካዩ ፍራኦል መንግስቱ ወደ ወላይታ ድቻ በውሰት ውል አምርቷል፡፡ አሳምነው አንጀሎን በተመሳሳይ የውሰት ውል ከድሬዳዋ ያገኘው ወላይታ ድቻ ፍራኦልን እስከ ውድድር ዘመኑ መጨረሻ ይጠቀምበታል፡፡

ዳንኤል መስፍን

ዳንኤል መስፍን

ይህንን ፅሁፍ ያቀረብኩላችሁ ዳንኤል መስፍን ነኝ

ከፎቶው በታች ያለው የፌስቡክ ምልክት ተጭነው ሊያገኙኝ ይችላሉ
ዳንኤል መስፍን

ዳንኤል መስፍን

ይህንን ፅሁፍ ያቀረብኩላችሁ ዳንኤል መስፍን ነኝ ከፎቶው በታች ያለው የፌስቡክ ምልክት ተጭነው ሊያገኙኝ ይችላሉ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *