የሊግ ውድድሮች እጣ የሚወጣባቸው ቀናት ታውቀዋል

የኢትየጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን በበላይነት የሚመራቸው የሊግ ውድድሮች ከመጀመራቸው በፊት የ2009 የውድድር ዘመን ግምገማ ፣ ስለ ቀጣይ አመት የሊጎቹ የአደረጃጀት (ፎርማት) ሁኔታ እና ደንቦች ላይ ጨምሮ የእጣ ማውጣት ስነስርዓቱን የሚያደርግበትን ቀን እና ቦታ ይፋ አድርጓል።

የወንዶች ፕሪምየር ሊግ መስከረም 15 እንዲሁም የሴቶቹ ፕሪምየር ሊግ በማግስቱ መስከረም 16 ሀዋሳ ላይ እንደሚደረግ ሲገለፅ የከፍተኛ ሊጉ እና የአንደኛ ሊጉ ደግሞ መስከረም 21 እና መስከረም 27 አዲስ አበባ ላይ እንደሚደረግ ለማወቅ ተችሏል። ከ20ዓመት በታች ፕሪምየር ሊግ ጥቅምት 15 ፣ ከ17ዓመት በታች ፕሪምየር ሊግ ጥቅምት 20 አዲስ አበባ ላይ እንደሚደረግ ፌደሬሽኑ ለሶከር ኢትዮጰያ ገልጿል።

ከዚህ ቀደም ስድስቱም የሊግ ውድድሮች የሚጀመሩበት ቀን ይፋ መሆኑ የሚታወስ ቢሆንም በተለይ የወንዶቹ ፕሪምየር ሊግ ይጀመራል ተብሎ ከተነገረው ጥቅምት 4 ቀን ተገፍቶ ሊደረግ እንደሚችልም እየተሰማ ይገኛል።

ሚካኤል ለገሰ

ሚካኤል ለገሰ

ይህንን ፅሁፍ ያቀረብኩላችሁ ሚካኤል ለገሰ ነኝ

ከፎቶው በታች ያለው የፌስቡክ እና ትዊተር ምልክትን ተጭነው ሊያገኙኝ ይችላሉ
ሚካኤል ለገሰ

ሚካኤል ለገሰ

ይህንን ፅሁፍ ያቀረብኩላችሁ ሚካኤል ለገሰ ነኝ ከፎቶው በታች ያለው የፌስቡክ እና ትዊተር ምልክትን ተጭነው ሊያገኙኝ ይችላሉ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *