ሴካፋ 2017፡ ቡሩንዲ ሳትጠበቅ ከዩጋንዳ ጋር ነጥብ ተጋርታለች

የሴካፋ ሲኒየር ቻሌንጅ ዋንጫ የምድብ ሁለት የመጀመሪያ ጨዋታ ካካሜጋ ላይ ሰኞ ተደርጎ በውድድሩ ላይ ለዋንጫ የምትጠበቀው ዩጋንዳ የቡሩንዲን የተከላካይ መስመር መስበር ተስኗት 0-0 ጨዋታዋን ለማጠናቀቅ ተገዳለች፡፡ የተቀዛቀዘ የመጀመሪያ 45 እንዲሁም በሙከራ የታጀበ ሁለተኛ 45 የጨዋታው መገለጫ ነበር፡፡

የዩጋንዳው አሰልጣኝ ሞሰስ ባሴና ሞሮኮ ለምታስተናግደው የቻን ውድድር ለመዘጋጀት ቡድናቸውን በአብዛኛው ያዋቀሩት ከዩጋንዳ አዛም ፕሪምየር ሊግ ባለድል ከሆነው ኬሲሲኤ ነው፡፡ ከ70 በመቶ በላይ የኳስ ቁጥጥር የነበራቸው ዩጋንዳዎች በብዛት ተጥቅጥቀው በመካላከልን እና መልሶ ማጥቃት ይጫወቱ የነበሩትን ቡሩንዲዎችን ለማሸነፍ ተስኗቸዋል፡፡ በመጀመሪያው አጋማሽ አለን ካታሬጋ ከሞከረው ሙከራ ውጪ ኢላማውን የጠበቀ ሙከራ እና የረባ እንቅስቃሴ ሳይደረግበት ተጠናቋል፡፡ ቲሞቲ አዎኒ ዩጋንዳን በግንባሩ ገጭቶ ባስቆጠረው ግብ ቀዳሚ ቢያደርግም ግቡ ሳይፀድቅ ቀርቷል፡፡

በሁለተኛው 45 ሁለቱም ቡድኖች ለማሸነፍ የነበራቸው ብርቱ ፍላጎትን ተከትሎ ጥሩ ፉክክር አሳይተዋል፡፡ አሁንም ዩጋንዳ የኳስ ቁጥጥር የባላይ የነበረች ቢሆንም ቡሩንዲ በቡኩንጉ ስታዲየም በተገደኘው ደጋፊ ታግዛ ለግብ የቀረቡ ሙከራዎችን ማድረግ ችላለች፡፡ ዩጋንዳ በሙዛሚሩ ሙቲያባ ከ25 ሜትር አክርሮ የሞከረውን ኳስ የቡሩንዲው ግብ ጠባቂ ጆናታን ናሂማና መልሶበታል፡፡ ብሩንዲ በበኩሏ በደቡብ አፍሪካ አብሳ ፕሪምየርሺፕ የካበደ ልምድ ያለውን ፊስተን አብዱልራዛክን በመጠቀም ሁለት ያለቀላቸውን እድሎች አምክናለች፡፡ ፊስተን በቀላሉ የዩጋንዳ ተከላካዮች በማለፍ ለቡድን አጋሮቹ የመቀባበያ እኛ የፈጣን መልሶ ማጥቃት አማራጮችን በመፍጠር በጨዋታው ጥሩ መንቀሳቀስ ችሏል፡፡

ብሩንዲ ጠንካራዋን ዩጋንዳን ነጥብ ማሳጣሏን ተከትሎ ምድቡን መምራት ችላለች፡፡ ዛሬ 9፡00 ላይ በዚሁ ምድብ የሚገኙት ኢትዮጵያ እና ደቡብ ሱዳን ይገናኛሉ፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *