የመቐለ እና ፋሲል ጨዋታ አዲስ አበባ ላይ ይደረጋል

በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ 26ኛ ሳምንት ከሚከናወኑ ጨዋታዎች መካከል አንዱ የሆነው የመቐለ ከተማ እና ፋሲል ከተማ ጨዋታ በገለልተኛ ሜዳ እንደሚካሄድ ይታወቃል።

በ26ኛው ሳምንት በሁለት ቀናት ውስጥ አራት ጨዋታዎች በአዲስ አበባ ስታድየም የሚካሄዱ በመሆኑ ጨዋታው በሰበታ ሊካሄድ መርሐ ግብር ወጥቶለት የነበረ ቢሆንም ከፌዴሬሽኑ ባገኘነው መረጃ የሰበታ ሜዳ ከወቅቱ ዝናባማ የአየር ሁኔታ ጋር በተያያያዘ ለጨዋታ አመቺ ባለመሆኑ እና በሁለቱም ክለቦች ጥያቄ መሠረት ወደ አዲስ አበባ ስታድየም መዞሩ ታውቋል።

ጨዋታው የቀን ለውጥ ሳይደረግበት ሰኞ ሰኔ 4 ቀን 2010 ረፋድ 04:00 ላይ የሚከናወን ይሆናል።

የ26ኛ ሳምንት መርሐ ግብር

ሰኞ ሰኔ 4 ቀን 2010

04:00 መቐለ ከተማ ከ ፋሲል ከተማ (አአ)

09:00 ቅዱስ ጊዮርጊስ ከ ወልዲያ (አአ)

09:00 ወልዋሎ ከ ደደቢት (ዓዲግራት)

09:00 አርባምንጭ ከ ወላይታ ድቻ (አርባምንጭ)

09:00 ሲዳማ ቡና ከ ድሬዳዋ ከተማ (ይርጋለም)

11:30 መከላከያ ከ ጅማ አባ ጅፋር (አአ)

ማክሰኞ ሰኔ 5 ቀን 2010

09:00 ኤሌክትሪክ ከ ሀዋሳ ከተማ (አአ)

11:30 ኢትዮጵያ ቡና ከ አዳማ ከተማ (አአ)