የፕሪምየር ሊጉ 26ኛ ሳምንት ላይ በድጋሚ የሰዓት ለውጥ ተደርጓል

በተደጋጋሚ የሰዓት ፣ የቦታ እና የቀን ለውጥ እያስተናገደ የሚገኘው የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ 26ኛ ሳምንት መርሐ ግብር በድጋሚ የሰዓት ለውጥ ተደርጎበታል። 

ፌዴሬሽኑ እንዳስታወቀው ማክሰኞ የሚደረጉት ጨዋታዎችን ሰዓት በማቀያየር 12:00 የነበረው የመከላከያ እና ጅማ አባጅፋር ጨዋታ ወደ 10:00 ሲቀየር 09:00 የነበረው የኢትዮጵያ ቡና እና አዳማ ከተማ ጨዋታ ወደ 12:00 ተቀይሯል።

አዲሱ መርሐ ግብር ይህንን ይመስላል

ሰኞ ሰኔ 4 ቀን 2010

04:00 መቐለ ከተማ ከ ፋሲል ከተማ (አአ)

09:00 ኤሌክትሪክ ከ ሀዋሳ ከተማ (አአ)

09:00 ወልዋሎ ከ ደደቢት (ዓዲግራት)

09:00 አርባምንጭ ከ ወላይታ ድቻ (አርባምንጭ)

09:00 ሲዳማ ቡና ከ ድሬዳዋ ከተማ (ሀዋሳ)

11:30 ቅዱስ ጊዮርጊስ ከ ወልዲያ (አአ)

ማክሰኞ ሰኔ 5 ቀን 2010

10:00 መከላከያ ከ ጅማ አባ ጅፋር (አአ)

12:00 ኢትዮጵያ ቡና ከ አዳማ ከተማ (አአ)