አቶ አብነት ገ/መስቀል በፊፋ ግብዣ ወደ ሩሲያ አቅንተዋል

የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ማኅበር ሊቀመንበር አቶ አብነት ገ/መስቀል በፊፋ በቀረበላቸው ግብዣ መሰረት የ2018 የሩሲያ ዓለም ዋንጫ ግማሽ ፍፃሜ እና የፍፃሜ ጨዋታዎችን ለመታደም ትላንት ወደ ሩሲያ አቅንተዋል። ትላንት ምሽትም በሴይንት ፒተርስበርግ ስታድየም በመገኝት ፈረንሳይ ከቤልጅየም ያደረጉትን ጨዋታ የተከታተሉ ሲሆን ከዚህ በኋላም ቀሪ ጨዋታዎችን እስከ ፍፃሜው ድረስ በተመሳሳይ መልኩ ጨዋታዎችን ይከታተላሉ ተብሎ ይጠበቃል ።

ቅዱስ ጊዮርጊስን በሊቀ መንበርነት የሚመሩት አቶ አብነት ገ/መስቀል በአፍሪካ እግርኳስ ኮንፌድሬሽን (ካፍ) ውስጥ የክለብ ውድድሮች ኮሚቴ አባል መሆናቸው ይታወቃል።