የሱራፌል ዳኛቸው ማረፊያ ፋሲል ሆኗል

የክረምቱ ዝውውር መስኮት ለፋሲል ከነማ የሰመረለት ይመስላል። በሊጉ በወቅታዊ ጥሩ አቋማቸው ላይ የሚገኙ ተጫዋቾችን እያስፈረሙ የሚገኙት አጼዎቹ ሱራፌል ዳኛቸውን 8ኛ ፈራሚ አድርገዋል። 

ባለፉት ሁለት ዓመታት በኢትዮጵያ እግርኳስ ላይ ብቅ ካሉ ባለ ተስጥዖ ተጫዋቾች መካከል አንዱ የሆነው ሱራፌል በ2008 ወደ ዋናው ቡድን ካደገ በኋላ በመጨረሻዎቹ ሁለት ዓመታት መደበኛ ተሰላፊ መሆን ችሏል። ሱራፌል በሁለት ዓመት ኮንትራት የተቀላቀለው ሱራፌል ከግራ መስመር ወደ ውስጥ በመግባት በሚፈጥራቸው የጎል እድሎች የሚታወቅ ተጫዋች ነው።