የኮፓ ኮካ ኮላ ሀገር አቀፍ ውድድር ነገ ይጀምራል

በኮፓ ኮካ ኮላ ኩባንያ አማካኝነት እድሜያቸው 15 ዓመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች የሚሳተፉበት ሀገር አቀፍ ውድድር በነገው እለት በባቱ ከተማ ይጀምራል። 

ለአራተኛ ጊዜ የሚካሄደው ይህ ውድድር በትምህርት ቤቶች እና በክልል አቀፍ ደረጃ ሲካሄድ የቆየ ሲሆን ከውድድሮቹ የተመለመሉ ታዳጊዎች ክልል እና የከተማ መስተዳድራቸውን የሚወክሉ ይሆናል። እስካሁን ባለው መረጃ መሠረትም ከትግራይ፣ ኢትዮ ሶማሌ እና ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ውጪ ሌሎች ክልሎች በውድድሩ ላይ እንደሚሳተፉ ተረጋግጧል። 

ዛሬ 10:30 ላይ በተከናወነው የእጣ ማውጣት ስነ-ስርዓት የፌዴሬሽኑ ጊዜያዊ ፀኃፊ አቶ ሰለሞን ገ/ሥላሴ እና ሌሎች የፌደሬሬሽን አመራር አካላት የተገኙ ሲሆን ስለ ውድድሩ ማብራርያ ተሰጥቷል። በወጣው እጣ መሰረትም የምድብ ድልድሉ ይህን ይመስላል:-

ወንዶች 

ምድብ ሀ: ኦሮሚያ፣ ድሬ ዳዋ፣ አፋር፣ አማራ

ምድብ ለ፡ ሐረሪ፣ ደቡብ፣ አዲስ አበባ፣ ጋምቤላ

የመጀመርያ ጨዋታዎች

ቅዳሜ ነሀሴ 19 ቀን 2010 

05:00 ኦሮሚያ ከ አማራ (ባቱ)

10:00 ድሬዳዋ ከ አፋር (ባቱ)

ሴቶች 

ምድብ ሀ፡ ድሬ ዳዋ፣ ኦሮሚያ፣ አዲስ አበባ፣ አፋር

ምድብ ለ፡ ጋምቤላ፣ ሐረሪ፣ ደቡብ፣ አማራ

የመጀመርያ ጨዋታዎች

ቅዳሜ ነሀሴ 19 ቀን 2010  

08:00 ድሬዳዋ ከ አፋር (ባቱ ት/ቤት)

10:00 ኦሮሚያ ከ አዲስ አበባ (ባቱ ት/ቤት)

ውድድሩ ከዚህ ቀደም በአዳማ፣ ቢሾፍቱ እና ጅግጅጋ የተካሄደ ሲሆን የኢትዮጵያ ወጣቶች ስፖርት አከዳሚ እና ሌሎች የታዳጊ ማሰልጠኛ ማዕከላት በርካታ ተጫዋቾችን መመልመል ችለዋል። በቅርቡ በአፍሪካ ሴቶች ዋንጫ ማጣርያ ከአልጄርያ ጋር በተደረገው ጨዋታ ከተመልካች አድናቆት የተቸራት አረጋሽ ከልሳን የመሳሰሉ ተጫዋቾችም ተገኝተውበታል። 

አምናው በኢትዮ ሶማሌ ክልል ጅግጅጋ ከተማ በተደረገው ውድድር በወንዶች ኢትዮ ሶማሌ፣ በሴቶች ደቡብ ክልል የዋንጫ ባለቤት መሆናቸው የሚታወስ ነው። 

ፎቶ (ከላይ) – የአምናው የወንዶች አሸናፊ ኢትዮ ሶማሌ