ሀሪስተን ሄሱ ባህር ዳር ከተማን ተቀላቀለ

በዝውውር መስኮቱ ጥሩ እየተንቀሳቀሰ የሚገኘው ባህር ዳር ከተማ ሀሪስተን ሄሱን አስፈርሟል። 

ቤኒናዊ የቀድሞ የድራገን ግብ ጠባቂ ሀሪስተን ወደ ኢትዮጵያ የመጣው በ2008 ክረምት ለኢትዮጵያ ቡና በመፈረም ሲሆን ለሁለት ዓመት በቡናማዎቹ ቤት ቆይታ ማድረግ ችሏል። ተጫዋቹ ከተለያዩ ክለቦች ጋር ስሙ ተያይዞ ቆይቶ በመጨረሻም ወደ ጣናው ሞገድ በአንድ ዓመት ውል መቀላቀሉን የታወቀ ሲሆን በዛሬው እለት ፊርማው በፌዴሬሽን ይፀድቃል ተብሏል።

ባህር ዳር ከተማ እስካሁን 8 አዳዲስ ተጫዋቾችን ሲያስፈርም ጃኮ አራፋት ወደ ኢትዮጵያ ሲመጣ ስምንተኛው ፈራሚ ሆኖ ቡድኑን የሚቀላቀል ይሆናል።