መቐለ ከተማ በሙከራ ላይ የነበሩ 3 ተጫዋቾችን አስፈረመ

በዝውውር መስኮቱ በስፋት ሲሳተፍ የቆየው መቐለ ከተማ ለአንድ ወር የሙከራ እድል ሰጥቷቸው የነበረው ኃይለዓብ ኃይለሥላሴ፣ ሙሉጌታ ወልደ ጊዮርጊስ እና አርዓዶም ገ/ህይወትን በቋሚነት አስፈርሟል።

ባለፈው ወር ከእንግሊዝ በመምጣት በመቐለ ከተማ የተሳካ የሙከራ ግዜ ያሳለፈው የቀድሞው የትራንስ፣ ኢትዮጵያ ቡና እና አየር ኃይል የአጥቂ ክፍል ተሰላፊ አርዓዶም ወደ ትውልድ ከተማው ተመልሶ ፊርማውን ያኖረ ሲሆን ከዘጠኝ ዓመታት በኋላ በፕሪምየር ሊጉ ዳግም ለመጫወት ተቃርቧል። ሌላው ለመቐለ ከተማ ፊርማውን ያኖረው የመሃል ሜዳ ተጫዋቹ ኃይለኣብ ኃይለሥላሴ ሲሆን ከዚህ በፊት ለወልዋሎ እና ደደቢት መጫወቱ ይታወሳል። በበርካታ ቦታዎች ላይ መጫወት የሚችለው የቀድሞው የመከላከያ፣ ወልድያ እና ኢኮስኮ ተጫዋች ሙሉጌታ ወልደጊዮርጊስ እንደ ሁለቱ ተጫዋቾች ሁሉ በአንድ ዓመት ውል ክለቡን ተቀላቅሏል።

ከመቐለ ከተማ የተያያዘ ዜና በዓመቱ መጀመርያ ውሉን አራዝሞ የነበረው የግራ መስመር ተከላካዩ ዳዊት ዕቑበዝጊ ከመቐለ ከተማ ጋር በስምምነት መለያየቱ ለማወቅ ተችሏል።