2018/19 ካፍ ቻምፒየንስ ሊግ ሙሉ ድልድል

የአፍሪካ እግርኳስ ኮንፌዴሬሽን በ2017 ባሳለፈው ውሳኔ መሰረት አህጉራዊ የክለብ ውድድሮች በአንድ የካላንደር ዓመት (ጃንዋሪ-ዲሴምበር) መካሄዳቸው ቀርቶ ከኦገስት-ሜይ በሚደረግ የውድድር አካሄድ መቀየሩ ይታወሳል፡፡ ዘንድሮ (2018) ለመጨረሻ ጊዜ በቀድሞው ፎርማት ተካሂዶም በትላንትናው ዕለት በኤስፔራንስ አሸናፊነት መጠናቀቁ ይታወሳል፡፡

አዲሱ የካላንደር ፎርማት ከቀጣዩ የውድድር ዘመን (2019/20) ጀምሮ ሙሉ ለሙሉ ተግባራዊ የሚደረግ ሲሆን ዘንድሮ ግን ከሁለት ሳምንት በኋላ ተጀምሮ ሜይ ወር ላይ የሚጠናቀቅ ይሆናል፡፡ ካለፉት ውድድሮች በተለየም ዘንድሮ ጨዋታዎች በተቀራራቢ የጊዜ ልዩነቶች ይካሄዳሉ፡፡

ካፍ ባሳለፍነው ሳምንት የቅድመ ማጣርያ እና የመጀመርያ ዙር ድልድል አውጥቶ የነበረ ቢሆንም ሙሉ ለሙሉ ይፋዊ በሆነ መንገድ በድረ-ገጹ ላይ ያስታወቀው በትላንትናው ዕለት ነበር፡፡ በድልድሉ መሰረት የኢትዮጵያው ቻምፒዮን ጅማ አባ ጅፋር ከጅቡቲው ቴሌኮም ጋር በቅድመ ማጣርያው ይጫወታል፡፡ የመጀመርያው ጨዋታ ጅቡቲ ላይ ሲከናወን የመልሱ ጨዋታ ደግሞ አዲስ አበባ ስታድየም ላይ የሚከናወን ይሆናል፡፡ አባ ጅፋር ይህንን ጨዋታ በድል ከተወጣ በመጀመርያው ዙር የ2018 የቻምፒየንስ ሊግ የፍጻሜ ተፋላሚው አል-አህሊን የሚገጥም ይሆናል፡፡


ሙሉ ድልድሉ ይህን ይመስላል፡-

ቅድመ ማጣርያ ዙር
የመጀመርያ ጨዋታ – ኅዳር 18-19
የመልስ ጨዋታ – ኅዳር 25-26

ቅድሚያ የተጻፉት ክለቦች የመጀመርያውን ጨዋታ በሜዳቸው ያደርጋሉ

ዲያራፍ🇸🇳 1 🇹🇬ዩኤስ ኮሮኪ
ኤኤስ ሳውራ🇩🇿 2 🇨🇮ኤስሲ ጋኞዋ
ኢቲሀድ ታንገር🇲🇦 3 🇹🇩ኢሌክት ስፖርት
ለሜ. ንጎዚ🇧🇮 4 🇪🇬ኢስማይሊ
ቦቦ ዲዮላሶ🇧🇫 5 🇨🇲ኮተን ስፖርት
ሶኒዴፕ🇳🇪 6 🇿🇲ዜስኮ ዩናይትድ
ኦ. ፓያሬትስ🇿🇦 7 🇸🇨ላይት ስታርስ
ቮልካን ክለብ🇰🇲 8 🇳🇦አፍሪካን ስታርስ
ኖውህዲቦ🇲🇷 9 🇱🇾አህሊ ቤንጋዚ
ሌኦኔስ ቪ.🇬🇶 10 🇿🇦መ. ሰንዳውንስ
ጎር ማሒያ🇰🇪 11 🇲🇼ቢግ ቡሌትስ
ዴሎም🇨🇲 12 🇳🇬ሎቢ ስታርስ
ዩዲ ሶንጎ🇲🇿 13 🇿🇲ንካና
ሲምባ🇹🇿 14 🇸🇿ም. ስዋሎውስ
ጅቡቲ ቴሌኮም🇩🇯 15 🇪🇹ጅማ አባጅፋር
ኮንስታንቲን🇩🇿 16 🇬🇲ጋምቴል
ኤል ሜሪክ🇸🇩 17 🇺🇬ቫይፐርስ
ስታደ ሴ.አፍረካኔ🇨🇫 18 🇲🇱ስታደ ማሊየን
አሴክ ሚሞሳ🇨🇮 19 🇬🇦ማንጋ ስፖርት
ታውንሺፕ ሮለርስ🇧🇼 20 🇱🇸ባንቱ
ኤፒአር🇷🇼 21 🇹🇳ክለብ አፍሪካን
አል ሒላል🇸🇩 22 🏴󠁴󠁺󠀰󠀷󠁿ጄኬዩ
አል ናስር🇱🇾 23 🇸🇸አል ሒላል ጁባ
ሆሮያ🇬🇳 24 🇱🇷ቢዋይ ኮንትሮለርስ
ፕ. ዲ. አጉስቶ🇦🇴 25 🇨🇬ኤኤስ ኦቶሆ
ሲናፕስ🇲🇬 26 🇿🇼ፕላቲኒየም

የመጀመርያ ዙር
የመጀመርያ ጨዋታ – ታህሳስ 5-7
የመልስ ጨዋታ – ኅታህሳስ 12-14

ቅድሚያ የተጻፉት ክለቦች የመጀመርያውን ጨዋታ በሜዳቸው ያደርጋሉ

ዋይዳድ ካሳ. 27 ጨዋታ 1 አሸናፊ
ጨዋታ 2 አሸናፊ 28 ጨዋታ 3 አሸናፊ
ጨዋታ 4 አሸናፊ 29 ጨዋታ 5 አሸናፊ
ቲፒ ማዜምቤ🇨🇩 30 ጨዋታ 6 አሸናፊ
ጨዋታ 7 አሸናፊ 31 ጨዋታ 8 አሸናፊ
ጨዋታ 9 አሸናፊ 32 ጨዋታ 10 አሸናፊ
ጨዋታ 11 አሸናፊ 33 ጨዋታ 12 አሸናፊ
ጨዋታ 13 አሸናፊ 34 ጨዋታ 14 አሸናፊ
አል አህሊ🇪🇬 35 ጨዋታ 15 አሸናፊ
ጨዋታ 16 አሸናፊ 36 ጨዋታ 17 አሸናፊ
ጨዋታ 18 አሸናፊ 37 ጨዋታ 19 አሸናፊ
ኤስ ቪታ🇨🇩 38 ጨዋታ 20 አሸናፊ
ጨዋታ 21 አሸናፊ 39 ጨዋታ 22 አሸናፊ
ጨዋታ 23 አሸናፊ 40 ጨዋታ 24 አሸናፊ
ጨዋታ 25 አሸናፊ 41 ጨዋታ 26 አሸናፊ