የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ የሚጀምርበት ቀን ለውጥ ተደረገበት

በኢትዮጵያ የሊግ ውድድር በሁለተኛ እርከን ላይ የሚገኘው የከፍተኛ ሊግ ውድድር ጥቅምት 21 በኢትዮጵያ ሆቴል የውድድሩን ፎርማት ከሁለት ምድብ ወደ ሶስት ምድብ በመለወጥ በተደረገ የዕጣ ማውጣት ስነ ስርዓት ኅዳር 16 እንዲጀመር መወሰኑ ይታወቃል።

ፌዴሬሽኑ በዕጣ ማውጣት ስነ ስርዓቱ ወቅት በክለቦች ምዝገባ አካሄድ ዙርያ ጥብቅ አቋም እንደያዘ እና ውድድሩ በተባለው ጊዜ እንደሚጀመር ተገልጾ የነበረ ቢሆንም ቅዳሜ ኅዳር 7 በነበረው ስብሰባ ውድድሩ ከሚጀምርበት ቀን አንድ ሳምንት መገፋቱ ታውቋል። በዚህም ኅዳር 16 እና 17 የነበረው ወደ ኅዳር 22 እና 23 ተቀይሯል። ምክንያቱ ደግሞ ቡድኖች የመመዝገቢያ ክፍያ ባለመክፈላቸው የሚል ነው። 

በክለቦች የምዝገባ ክፍያ መዘግየት ምክንያት የከፍተኛ ሊጉ ውድድር አምናም በተመሳሳይ በተቆራረጠ ሁኔታ ዘግይቶ እንደተጀመረ የሚታወስ ሲሆን በሌሎች ሊጎች ላይም ይህ ችግር ተደጋግሞ ሲታይ ይስተዋላል።