የቻን አስተናጋጅነት ከኢትዮጵያ ተነጥቆ ለካሜሩን ተሰጠ

ኢትዮጵያ በጥር 2020 የሀገር ውስጥ ሊጎች የሚጫወቱ ተጫዋቾች ብቻ የሚሳተፉበት የአፍሪካ ሀገራት ዋንጫ (ቻን) ለማስተናገድ ከሁለት ዓመታት በፊት እድሉ ቢሰጣትም ውድድሩን ለማዘጋጀት ዝግጁ አለመሆኗን መገለፁን ተከትሎ ለካሜሩን ተላልፎ ተሰጥቷል።

ባሳለፍነው ወር መጀመርያ ይህን ውድድር ያስተናግዳሉ ተብለው የተለዩት ስታዲየሞችን ጨምሮ አጠቃላይ ለውድድሩ የሚያስፈልጉ ቅድመ ሁኔታዎች ከካፍ በተላኩ ባለሙያዎች አማካኝነት በተጎበኙበት ወቅት ያልተሰሩ በርካታ ስራዎች እንዳሉ መጠቆሙ የሚታወስ ሲሆን መንግስትም ለውድድሩ ዝግጅት የሚያስፈልገውን ወጪ ለመሸፈን ዝግጁ አለመሆኑ ሲገለፅ ቆይቷል።

ይሆን ተከትሎ የአፍሪካ እግርኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ) ባሳለፈው ውሳኔ መሠረት የአስተናጋጅነት እድሉን ከኢትዮጵያ መንጠቅ ለምዕራብ አፍሪካዊቷ ሀገር ካሜሩን ሰጥቷል። ካሜሩን የ2019 የአፍሪካ ዋንጫን የማስተናገድ እድሉን አግኝታ የነበረ ቢሆንም በተቀመጠው ጊዜ ዝግጅቷን የማጠናቀቅ አቅሟ ጥባቄ ውስጥ መግባቱን ተከትሎ ለግብፅ መሰጠቱ የሚታወስ ነው።


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡