የደደቢት እና ጅማ አባጅፋር ጨዋታ ተራዘመ

እሁድ ከሚደረጉት የ21ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ መርሃ ግብሮች አንዱ የነበረው የደደቢት እና ጅማ አባጅፋር ጨዋታ በደደቢት ጥያቄ ላልታወቀ ግዜ ተራዝሟል።

የደደቢት ተጫዋቾች ከሁለት ቀን በፊት በፋይናንስ ችግር ምክንያት ልምምድ ማቆማቸውን ተከትሎ በዚህ ሳምንት ከጅማ አባጅፋር ጋር ሊያደርጉት የነበረው ጨዋታ እንዲራዘም ቡድኑ ጥያቄ ባቀረበው መሰረት ነው ላልታወቀ ጊዜ የተራዘመው። በዚህ ዓመት በበርካታ የፋይናንስ ችግሮች ተከበው ውድድራቸው እያካሄዱ የሚገኙት ሰማያዊዎቹ ከዚህ ቀደምም በተመሳሳይ ችግር ምክንያት ልምምድ አቁመው እንደነበር ይታወሳል።

ይህ ጨዋታ ከሁለተኛው ዙር መጀመር በኋላ ከመደበኛ መርሐ ግብሩ የተራዘመ ሁለተኛው ጨዋታ መሆን ችሏል።


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡