በዋልታ ፖሊስ እግር ኳስ ክለብ ላይ ጥቃት ደረሰ

ዋልታ ፖሊስ ትግራይ የእግር ኳስ ክለብ ዛሬ ጠዋት ባልታወቁ ታጣቂዎች ጥቃት እንደደረሰበት ለማወቅ ተችሏል።

በአንደኛ ሊግ ተሳታፊ የሆነው ዋልታ ፖሊስ ትግራይ ከሰሜን ሸዋ ደብረብርሃን ጋር ጨዋታ አድርጎ ወደ መቐለ ሲመለስ በጉዞ ላይ እያለ ነበር በአፋር ክልል ገዋኔ አካባቢ ባልታወቁ ታጣቂዎች ጥቃት የደረሰባቸው። እስካሁን ባለሁ ሁኔታም በአንድ የቡድኑ አባል ላይ የሞት አደጋ መድረሱ ሲረጋገጥ በስምንት የቡድኑ አባላት ላይም ከበድ ያለ ጉዳት መድረሱን የቡድኑ መሪ ለትግራይ ቴሌቪዥን ገልፀዋል።

በኮንስታብል ዮሃንስ ሲሳይ የሚመራው ዋልታ ፖሊስ በ1960ዎቹ የተመሰረተ አንጋፋ ክለብ ሲሆን በጥቃቱ ዙርያ እስካሁን የተሰጠው ይፋዊ መግለጫ የለም።


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡