ፌዴሬሽኑ ወላይታ ድቻን ይቅርታ ጠየቀ

የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ከፋሲል ከነማ በደረሰው የተጫዋች ተገቢነት ክስ መሰረት ወላይታ ድቻ ላይ ትላንት ቅጣት መጣሉ የሚታወስ ነው። ሆኖም ዛሬ ውሳኔውን በድጋሚ ተመልክቶ እንደሻረው መግለፃችን ይታወሳል።

አሁን ደግሞ ፌዴሬሽኑ ለክለቡ በላከው ደብዳቤ ዝርዝር ጉዳዩን ጠቅሶ እርምት እንዲወሰድ፤ ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር ያደረጉት ጨዋታ 2-0 ውጤት እንዲፀድቅ መወሰኑን ገልጿል። ለተፈጠረው ስህተትም ይቅርታ ጠይቋል።

ደብዳቤው ይህን ይመስላል


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡

error: