ወላይታ ድቻ ለተጫዋቾች ጥያቄ ምላሽ ሰጠ

በሁሉም የሀገሪቷ የሊግ ውድድሮች የደሞዝ አልተከፈለንም ጥያቄ በበረታበት በዚህ ሰዓት የወላይታ ድቻ በተጫዋቾች በኩል ለተነሳበት ጥያቄ ምላሽ ሰጥቷል።

ያለፉትን ዓመታት ለተጫዋቾች ደሞዝ በመክፈል ረገድ አስተጓግሎ የማያውቀው ወላይታ ድቻ ስሙ ከተጫዋቾች ደሞዝ ክፍያ ጋር ባለፉት ሳምንታት መነሳቱ ይታወሳል። በዛሬው ዕለትም ተጫዋቾቹ ላቀረቡት ቅሬታ ምልሽ የሰጠው ክለቡ የሚያዚያ እና የግንቦት ወር ደሞዝ መክፈሉን ክለቡም፣ ተጫዋቾቹም ለሶከር ኢትዮጵያ ማረጋገጫ ሰጥተዋል። የዚህን ወር ደሞዝም በወሩ መጨረሻ እንደሚከፍል ክለቡ አሳውቋል።

በሌላ ዜና እስካሁን አስተዋሽ ያጡት ጅማ አባጅፋር፣ ወልዋሎ፣ ሱሑል ሽረ እና ሀዲያ ሆሳዕና ከፕሪምየር ሊግ ክለቦች ውስጥ እስካሁን ክፍያ ያልፈፀሙ መሆናቸው ሲታወቅ። አብዛኛው የከፍተኛ ሊግ እና የሴቶች ቡድኖች ተጫዋቾች ከደሞዝ ጋር ተያይዞ በከፍተኛ ማማረር ውስጥ እንደሚገኙ ለማወቅ ችለናል።

👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!


© ሶከር ኢትዮጵያ

error: