መቐለ 70 እንደርታዎች የወሳኝ ተጫዋቻቸው ውል ለማራዘም ተስማሙ

የነባር ተጫዋቾች ውል በማራዘም እና አዳዲስ ተጫዋቾች በማስፈረም የተጠመዱት መቐለዎች ከሳምንታት ድርድር በኋላ የአጥቂ አማካያቸው ያሬድ ከበደን ውል አራዝመዋል።

የእግር ኳስ ሕይወቱን በትውልድ ከተማው ራማ ጀምሮ ለከፍተኛ ሊጉ አክሱም ከተማ ሲጫወት በመቆየት በ2009 ወደ መቐለ 70 እንደርታ በማምራት ከክለቡ ጋር አስደናቂ አራት ዓመታት ያሳለፈው ይህ ተጫዋች ክለቡ ወደ ፕሪምየር ሊጉ እንድያድግ እና በ2011 የሊጉን ዋንጫ እንዲያነሳ ካስቻሉ ወሳኝ ተጫዋቾች አንዱ ነው።

በክለቡ በቆየባቸው ዓመታት በተለያዩ ቦታዎች ተሰልፎ የተጫወተው እና ከአማኑኤል ገ/ሚካኤል ጋር በፈጠረው ጥምረት በቀላሉ በደጋፊዎች ዓይን የገባው ያሬድ ውሉን ማራዘሙ ለክለቡ ጥሩ ዜና ነው።

👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!


© ሶከር ኢትዮጵያ

error: