የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት አቶ ኢሳይያስ ጂራ ቀጣይ የሊጉን አካሄድ በተመለከተ ተከታዩን ማብራሪያ ሰጥተዋል።
“በሀገራችን ያለውን የፋሲሊቲ ጉዳይ ልክ ነው እንረዳለን። አሁንም በሚከናወነው ሊግ የልምምድ ሜዳ ችግር እንዳለ እንሰማለን። ግን ደግሞ ነገሮችን ባላንስ አድርጎ መሄድ ያስፈልጋል።
“ሊጉ በምን መልኩ (ፎርማት) ይቀጥላል የሚለውን እየተነጋገርን ነው። ይሄ አካሄድ ከኮቪድ በኋላ ነው የሆነው። ከዛ በኋላ ፎርማቱ በዛው ቆሟል። አሁን ባለው ተጨባጭ ሁኔታ በሜዳ እና ከሜዳ ውጪ የማታከናውንባቸው ሁኔታዎች አሉ። በቀጣይ በኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬችን ስር የሚደረጉ ውድድሮች እንዳለፉት አመታት በአንድ ቦታ አይከናወኑም። ክለቦች የሚቀርባቸውን የተሻለ ሜዳ አስመዝግበው እየተመላለሱ የሚጫወቱበትን መንገድ እያመቻቸን ነው። ሊጉንም በተመለከተ ንግግር እያደረግን ነው።” በማለት የሊጉ ቅርፅ ለውጥ ሊደረግበት እንደሚችል ጥቆማ አድርገዋል።
በተያያዘ የሊጉ ክለቦች ቁጥር ከፍ በማለቱ ክለቦች ላይ የፋይናንስ ጫና በማምጣቱ ፌዴሬሽኑ የገንዘብ ድጎማ ሊያረግ ይችላል ወይስ የሚለውን ጥያቄ በተመለከተ የፌዴሬሽኑ ፕሬዝዳንት ይሄንን አይነት ተግባር ፌዴሬሽኑ እንደማያከናውንና የተሰማራበት አላማ እንደማያስኬደው ተጠቁሟል።