በወቅታዊ የእግርኳስ ጉዳይ ላይ የተሰጠው ጋዜጣዊ ተጠናቋል

በወቅታዊ የእግርኳስ ጉዳይ ላይ የተሰጠው ጋዜጣዊ ተጠናቋል

የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌደሬሽን የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ የክፍያ ስርዓቱን የጣሱ ክለቦችን የተመለከቱ ውሳኔዎች በተመለከተ የተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫን በተመለከተ ከስር ከስር ሀሳቦችን እያጋራን የነበረ ሲሆን መገባደጃ ላይ የተነሱ ሀሳቦችን ጠቅለል አድርገን አስቀምጠናል።

የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት አቶ ኢሳይያስ ጅራ ከመገናኛ ብዙሃን አባላት ለተነሳላቸው ጥያቄዎች ምላሽ ሲሰጡ ያነሷቸው አንኳር ሀሳቦች እንደሚከተለው አስቀምጠናል።

– ሁሉም ክለቦች ምን ያህል ንፁ እንደሆኑ ሲመረመሩ ነው የምናቀው።

– የፍርድ ቤት ጣልቃ ገብነት ከመጣ ለምን እኛ እንሰራም በሚል ነበር የፋይናንስ ስርዓቱን የሚያጣራው አካል ስራውን አቁሞ የነበረው።

– እነዚህ ክለቦች ነጥብ የተቀነሰባቸው አካሄዱን ጥሰው ወደ መደበኛ ፍርድ ቤት ስለሄዱ ነው። መቐለ 70 እንደርታ ነጥብ ያልተቀነሰበት ወደ መደበኛ ፍርድ ቤት ስላልሄደ ነው።

– የፋይናንስ ስርዓቱን በተመለከተ በዚሁ ዓመት ተጣርቶ ማለቅ ሲገባው አልሆነም።

– ይህ ደንብ የተወሰነ መሻሻል ያለበት ነገር አለ። መረሳት የሌለበት ይሄ ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ ደንብ ነው።

– የኢትዮጵያ ዋንጫን በተመለከተ አታስገባ ተብሎ ተጫዋች ባያስገባ ኖሮ እዚህ ጣጣ ውስጥ አይገባም ነበር።

– ማቻቻል ነው የተባለውን በተመለከተ ኢንዱስትሪውን ማየት ያስፈልጋል። አሁን የተገኘባቸውን አውርዶ ነገ ሌሎች ክለቦች ቢገኙ የሚፈጠረው ነገር ከባድ ነው።

– አልቀበልም ያለ ክለብ ሊጉን ትቶ መውጣት ይችላል ፤ መብቱ ነው።

– ለሚመጣው ነገር ተገዢ ነን። የጣስነው ህግ ካለ ለሚመጣው ነገር ምላሽ እንሰጣለን።

– መብቴን አስከብራለው ፤ የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን በድሎኛል የሚል አካል ካለ ወደሚመለከተው አካል መሄድ ይችላል።