ኢትዮጵያዊው አሰልጣኝ ወደ ታንዛንያው አዛም አቀንቷል።
ላለፈው አንድ ዓመት በሱዳኑ ታላቅ ክለብ አል ሂላል በምክትል አሰልጣኝነት ያገለገለው አዲስ ወርቁ ወደ ታንዛንያው ክለብ አዛም አቅንቷል።
ሁለት የፕሪሚየር ሊግ ዋንጫዎችን ባነሳበት የፈረሰኞቹ የስድስት ዓመታት ቆይታው እንዲሁም በዩጋንዳ እና ዛምቢያ በተለያዩ የስራ መደቦች ማገልገል የቻለው ይህ ወጣት አሰልጣኝ በውጤታማው አንድ ዓመት የሱዳኑ ክለብ ቆይታው የፍሎረንት ኢቤንጌ ምክትል አሰልጣኝ ሆኖ ሲሰራ መቆየቱ ሲታወስ አሁን ደግሞ ከአሰልጣኝ ፍሎረንት ኢቤንጌ ጋር በድጋሚ ለመስራት የታንዛንያውን ክለብ ተቀላቅሏል።