ዋልያዎቹ ነገ የልምምድ ጨዋታ ሊያደርጉ ነው

ዋልያዎቹ ነገ የልምምድ ጨዋታ ሊያደርጉ ነው

ለዩናይትድ ስቴትሱ ጉዞ ዝግጅት በማድረግ ላይ የሚገኙት ዋልያዎቹ ነገ ረፋድ የልምምድ ጨዋታ ሊያደርጉ ነው።

ሐምሌ 26 ከዲሲ ዩናይትድ ጋር ላለበት የኢግዚብሽን ጨዋታ ዝግጅቱን በማድረግ ላይ የሚገኘው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ምንም እንኳን በጋዜጣዊ መግለጫው ላይ ባይገለፅም ሶከር ኢትዮጵያ እንዳገኘችው መረጃ ከሆነ ነገ የልምምድ ጨዋታ ሊያደርግ መሆኑን አውቃለች።

በነገው ዕለት 3፡00 ላይ በአዲስ አበባ ስታዲየም ከ’ስሪ ፖይንት’ አካዳሚ ጋር የልምምድ ጨዋታ የሚያደርግ ሲሆን ስሪ ፖይንት ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን ጋር በመተባበር ሃያት በሚገኘው የልህቀት ማዕከት ያለፉትን ዓመታት ታዳጊዎችን በማቀፍ የማብቃት ስራ እየሰራ የሚገኝ አካዳሚ ነው።

ብሄራዊ ቡድኑ ነገ አመሻሽ ላይ 31 የልዑካን ቡድን በመያዝ ወደ ዩናይትድ ስቴትስ የሚያቀና ይሆናል።