👉 “ከይግባኝ ሰሚ ኮሚቴ ውሳኔ በኋላ ወደ መደበኛ ፍድብ ቤት መሄድ አይቻልም” አቶ ኢሳያስ ጅራ

👉 “ከይግባኝ ሰሚ ኮሚቴ ውሳኔ በኋላ ወደ መደበኛ ፍድብ ቤት መሄድ አይቻልም” አቶ ኢሳያስ ጅራ

👉”የደጋፊን ጫና መቋቋም ሲያቅታቸው ወደ ፌዴሬሽኑ ማስተላለፍ ተገቢ አይደለም

👉 “የሲዳማ ቡና አሰራሩን ተከትሎ ወደ ካስ በመሄዲ ትልቅ ክብር አለን ምሳሌም ይሆናል”

👉 “ከይግባኝ ሰሚ ኮሚቴ ውሳኔ በኋላ ወደ መደበኛ ፍርድ ቤት መሄድ አይቻልም።” አቶ ኢሳያስ ጅራ

የሲዳማ ቡና ይግባኝ እንዲቋረጥ ዓለም አቀፍ የስፐርት ገላጋይ ፍርድ ቤት የወሰነውን ውሳኔ አስመልክቶ ፕሬዝደንቱ አቶ ኢሳያስ ጅራ ምን አሉ


የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌሬሽን የሰሞንኛ ጉዳይ የሆነው እና ዓለም አቀፉ የስፖርት ገላጋይ ፍርድቤት የሲዳማ ቡና ይግባኝ እንዲቋረጥ ውሳኔ መስጠቱ ተከትሎ ። ያለውን ሂደት አስመልክቶ አቶ ኢሳያስ ጅራ ካዛንቺስ በሚገኘው ጁፒተር ሆቴል ላይ ለመገናኛ ብዙሃና ማብራሪያ እየሰጡ ይገኛል። ሲዳማ ቡና ወደ ካስ የሄደበት ሂደት እና የመጨረሻውን ውሳኔ ተከትሎ ለቀጣይ ሊሰጥ የሚችለውን ትምህርት ምን መሆን እንዳለበት ተናግረዋል።

አቶ ኢሳያስ በቅድሚያ ሰፊ ጊዜ ሰጥተው የተናገሩት በሲዳማ እና በፌዴሬሽኑ መካከል በካስ የነበረውን ሂደት በሰፊው ካብራሩ በኋላ ይህ የካስ ውሳኔ ለሌሎቹ ክለቦች ትምህርት ሰጥቶ እንደሚያልፍ ሲናገሩ ” በኢትዮጵያ እግርኳስ ውስጥ አንድ የፍትህ አካል ነው ያለው። ይህም አካል በጠቅላላ ጉባኤ የሚመረጥ ገለልተኛ ውሳኔ ሰጪ ኮሚቴ ነው። ፕሬዝደንቱ ወይም ሾል አስፈፃሚው የሚያዘው ጣልቃ የሚገባበት አይደለም። ስለዚህ የይግባኝ ሰሚ ኮሚቴ የሚሰጡ የመጨረሻ ውሳኔን አልፎ ወደ መደበኛ ፍርድ ቤት በመሄድ፣ ማሳገድ አይቻልም። ይግባኝ ሰሚ ኮሚቴ ቢሳሳት እንኳን ወደ ካስ መሄድ እንጂ የእግርኳን ሀሳብ መደበኛ ፍርድ ቤት መሄድ ተገቢ አይደለም። ሲዳማ ቡና በዚህ ረገድ ቅሬታውን ወደ ካስ በመሄዱ ትልቅ ክብር አለን ለሌሎችም ክለቦች ትምህር የሚሰጥ ነው። የስፖርት ውሳኔን ወደ መደበኛ ፍርድ ቤት ከዚህ በኋላ መውሰድ እንደማይቻል ማሳያነው ብለዋል።”

ክለቦች የራሳቸውን ስህተት የደጋፊን ጫና መቋቋም ሲያቅታቸው ፌዴሬሽኑ ለአንድ ወገን እንደቆመ አድርጎ በማሰብ ትክክል አይደለም። አስቀድሞ እራሳቸው ተስማምተው ያወጡት ህግን ማክበር ያስፈልጋል። ራሳቸው የጣሱትን ህግና ወይም ጥፋትን በማረም መሄድ እንጂ የደጋፊን ጫና መቋቋም ሲያቅታቸው ወደ ፌዴሬሽኑ ማስተላለፍ ተገቢ አይደለም። ካሉ በኋላ አክለውም ውሳኔ “የአሸናፊነት እና የተሸናፊነት ስነ ልቦና ሊኖር አይገባም ፌዴድዴሽኑ ይህን በመርታቱ የበላይነት እንዳይሰማው እንዲሁም ሲዳማ ቡና ጥያቄው ውድቅ በመሆኑ የተሸናፊነት ስሜት እንዳይሰማው።”በማለት ገልፀዋል።