ባህር ዳር ከተማ የመስመር ተጫዋቹን ውል አራዝሟል

ባህር ዳር ከተማ የመስመር ተጫዋቹን ውል አራዝሟል

የአሠልጣኝ ደግአረገን ውል ለማራዘም የተስማማው ባህር ዳር ከተማ የመስመር ተከላካዩን ውል ለተጨማሪ ዓመት አራዝሟል።

በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት በ54 ነጥቦች ሦስተኛ ደረጃን ይዞ ያጠናቀቀው ባህር ዳር ከተማ ዘግየት ብሎ ወደ ዝውውሩ ለመግባት የወሰነ ሲሆን አዳዲስ ተጫዋቾችን ከማራዘሙ በፊትም የነበሮቹን ውል ማራዘም ጀምሯል።

በዚህም የቀድሞ የወላይታ ድቻ ተጫዋች የነበረው መሳይ አገኘው ያለፉትን ሦስት ዓመታት በውሃ ሰማያዊው ማሊያ ያሳለፈ ሲሆን አሁንም ለተጨማሪ ዓመት በክለቡ ለመቆየት ስምምነት ፈፅሟል።