ቅደመ ዝግጅታቸውን የጀመሩት ኢትዮጵያ ቡናዎች አምስተኛ ፈራሚያቸውን አግኝኝተዋል።
በአሰልጣኝ አብይ ካሳሁን እየተመሩ ቅድመ ዝግጅታቸውን በአዳማ ከተማ የጀመሩት ቡናማዎቹ ናይጄሪያዊ አጥቂ አዳሙ አቡበከር እንዲሁም በረከት ብርሀነ እና ዘላለም አባቴን የግላቸው ሲያደርጉ በመቀጠልም የቡድናቸው አምስተኛ ፈራሚ የሆኑትን ግብጠባቂ እንደሻው እሸቴ እና አማካይ ፉአድ ኢብራሂምን ማስፈረማቸው አረጋግጠናል።
ፉአድ በአዳማ ተስፋ ቡድን እስከ ዋናው ቡድን የተጫወተ ሲሆን በኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድንም አሳልፏል። በተጠናቀቀው የውድድር ዓመትም ለአዳማ ከተማ በአመዛኙ ጨዋታዎች የተሳተፈ ሲሆን አሁን መዳረሻውን ኢትዮጵያ ቡና አድርጓል።
የግብ ዘቡ እንደሻው እሸቴ በወላይታ ድቻ ከተስፋ እስከ ዋና ቡድን መጫወት ሲችል በቀመጠል በ2016 ወደ የካ ክፈለ ከተማ የአንድ ዓመት ቆይታ አድርጎ ዳግም ወደ ወላይታ ዲቻ ቢመለስም በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት ከሀላበ ከተማ ጋር መልካም የሚባል ጊዜ አሳልፎ አሁን ወደ ቡናማዎቹ አምርቷል።