ወጣቱ አማካይ ወደ ሻምፒዮኖቹ አምርቷል

ወጣቱ አማካይ ወደ ሻምፒዮኖቹ አምርቷል

የወቅቱ የሊጉ አሸናፊ ኢትዮጵያ መድን ወጣቱን አማካይ የግላቸው አድርገዋል።

ለሀጉራዊ እና ለሀገር ለውስጥ ውድድሮች ቅድመ ዝግጅታቸውን ከጀመሩ ቀናቶች ያስቆጠሩት መድኖች የአምስት ነባር እና ብሩክ ሙልጌታን አዲስ ዝውውር ማጠናቀቃቸው ይታወሳል። በቀጣይ ቀናት ተጨማሪ አዳዲስ ተጫዋቾች ወደ ስብስባቸውን የሚቀላቅሉት መድኖች በመቀጠል ወጣቱን አማካይ ሙሴ ኪሮስን ለማስፈረም ተስማምተዋል።

አዳማ ከተማ ላይ በተካሄደው የአንደኛ ሊግ ማጠቃለያ ውድድር ላይ ለአሶሳ ከተማን ወክሎ ባሳየው መልካም እንቅስቃሴ ወደ አዳማ ከተማ በማምራት ያለፉትን ሁለት ዓመት ያገለገለ ሲሆን ዘንድሮ ለቡድኑ በነበረው ቆይታ በ28 ጨዋታዎች ተሰልፎ 2030 ደቂቃዎች ቡድኑን ያገለገለው ወጣቱ አማካይ አሁን ለሻምፒዮኖቹ ለሁለት ዓመት ለመጫወት መስማማቱን አውቀናል።