ኃይቆቹ ወደ ዝውውሩ በመግባት አንድ ተጫዋች የግላቸው አድርገዋል።
አሰልጣኝ ተመስገን ዳናን ዋና አሰልጣኝ አድረገው የሾሙት ሀዋሳ ከተማዎች ዛሬ በይፋ ወደ ዝውውሩ በመግባት ቁመታሙን አማካይ አብነት ደምሴን ማስፈረማቸው እርግጥ ሆኗል።
በወላይታ ድቻ የእግርኳስ ህይወቱን እንደጀመረ የሚታወቀው አማካዩ በኢትዮ ኤሌክትሪክ ፣ ኢትዮጵያ ቡና እና ያለፉትን ሁለት ዓመታት በወላይታ ድቻ ቆይታ ያደረገ ሲሆን ዘንድሮ በነበረው ቆይታ በ26 ጨዋታዎች ተሰልፎ 2225 ደቂቃዎችን በሜዳ ላይ በማሳለፍ አሁን መዳረሻውን ወደ ኃይቆቹ አድርጎ ለሁለት ዓመት ፊርማውን አኑሯል።
አሰልጣኝ ተመስገን ዳና በቀጣዮቹ ቀናት ተጨማሪ ተጫዋቾችን ወደ ቡድናቸው እንደሚቀላቅሉ ይጠበቃል።