በቅዱስ ጊዮርጊስ ቤት ያለፈውን ሁለት ዓመት ያገለገለው አጥቂ ወደ ኢትዮጵያ መድን አምርቷል።
በአዳማ ከተማ ቅድመ ውድድር ዝግጅታቸውን በአቋም መፈተሻ ጨዋታዎችን አጅበው እየተዘጋጁ የሚገኙት ኢትዮጵያ መድኖች የአምስት ወሳኝ ተጫዋቾቻቸውን ውል በማራዘም የሁለት ተጫዋቾችን ዝውውር በማጠናቀቃቸው ይታወቃል። አሁን ደግሞ አጥቂውን አማኑኤል ኤርቦን ለማስፈረም መቃረባቸውን አውቀናል።
አማኑኤል ያለፉትን ሁለት ዓመታት ከፈረሰኞቹ ጋር ቆይታ ሲያደርግ በተለይ በተጠናቀቀው የውድድር ዘመን ለቡድኑ ባደረጋቸው 30 ጨዋታዎች 2104 ደቂቃዎች ተሳትፎ በማድረግ ሰባት ጎሎችን በማስቆጠር ያገለገለ ሲሆን ከዚህ ቀደም
በአርባምንጭ ከተማ ደደቢት ከሚባል ፕሮጀክት የተገኘው አማኑኤል በጎፋ ባረንቼ እና በለገጣፎ ለገዳዲ፣ በቅዱስ ጊዮርጊስ ካሳለፈ በኋላ አሁን ለአንድ ዓመት ቆይታ ማረፊያውን ኢትዮጵያ መድን አድርጓል።