ቅዱስ ጊዮርጊሶች የመሃል ተከላካዩን የግላቸው አድርገዋል

ቅዱስ ጊዮርጊሶች የመሃል ተከላካዩን የግላቸው አድርገዋል

በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት በስሑል ሽረ ቆይታ የነበረው ተጫዋች ወደ ፈረሰኞቹ አቅንቷል።

በአሰልጣኝ ፋሲል ተካልኝ መሪነት ለ2018 የውድድር ዓመት አዳዲስ ተጫዋቾች በማስፈረም እና የነባሮቹን ውል በማራዘም በዝግጅት ላይ የሚገኙት ፈረሰኞቹ ቀደም ብለው አጥቂውን ቡአይ ኩዌት፣ አማካዩ አበባየሁ ዮሐንስ ፣ የመስመር ተከላካዩ መሳፍንት ጳውሎስን በማስፈረም የተገኑ ተሾመን ውል ማራዘማቸው ሲታወስ አሁን ደግሞ ባለፈው የውድድር ዓመት በስሑል ሽረ ቆይታ የነበረው ተከላካዩ ጥዑመልሳን ኃይለሚካኤልን አስፈርመዋል።

ባለፈው የውድድር ዓመት በ27 ጨዋታዎች ተሳትፎ
2312′ ደቂቃዎች ቡድኑን ያገለገለው ግዙፉ ተከላካይ ከዚህ ቀደም በሺንሺቾ፣ ስልጤ ወራቤ፣ ደደቢት፣ ቤንጂ ማጂ ቡና እንዲሁም በተጠናቀቀው የውድድር  ዓመት በስሑል ሽረ መጫወቱ ይታወሳል።