ባለፉት ዓመታት በአዞዎቹ ቆይታ የነበረው ተጫዋች ወደ ቢጫዎቹ ለማምራት ከስምምነት ደርሷል።
በአሰልጣኝ ግርማ ታደሰ የሚመሩት ወልዋሎዎች ለቀጣይ ውድድር ዓመት እያደረጉት ባለው እንቅስቃሴ ከዚህ ቀደም ፍሬው ሰለሞን፣ በየነ ባንጃው፣ ኢብራሂም መሐመድ፣ ፍሬዘር ካሳ፣ ሰመረ ሀፍታይ እና ጌትነት ተስፋዬን ለማስፈረም መስማማታቸው የሚታወስ ሲሆን አሁን ደግሞ የመስመር አጥቂው ፍቃዱ መኮንን ለማስፈረም ከስምምነት ደርሰዋል።
የእግር ኳስ ሂወቱ በጋሞ ጨንቻ ጀምሮ በወላይታ ድቻና በአርባምንጭ ከተማ ቆይታ የነበረው ተጫዋቹ በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት በ23 ጨዋታዎች ተሳትፎ 1128′ ደቂቃዎች ቡድኑን ያገለገለ ሲሆን አሁን ደግሞ ቢጫዎቹን ለመቀላቀል ተስማምቷል።