ሸገር ከተማ ተከላካይ አስፈርሟል

ሸገር ከተማ ተከላካይ አስፈርሟል

ከኢትዮጵያ ቡና ጋር ቆይታ የነበረው ተከላካይ ማረፊያው ሸገር ከተማ ሆኗል።

ጠንከር ያሉ ዝውውሮችን በመፈፀም ወደ ሊጉ ብቅ ያሉት ሸገር ከተማዎች በርከት ያሉ ዝውውሮችን እየፈፀሙ ሲሆን አሁን ደግሞ ሁለገቡን ተከላካይ ገዛኸኝ ደሳለኝን ማስፈረማቸው እርግጥ ሆኗል።

የእግርኳስ ሕይወቱን በክለብ ደረጃ በኢትዮጵያ ቡና ከታዳጊ እስከ ዋናው ቡድን መጫወት የቻለ ሲሆን ወደ ሻሸመኔ ከተማ እንዲሁም በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በአንድ ወቅት ተጫውቶ የነበረው ተከላካዩ በድጋሚ ወደ አሳዳጊው ቡድን ቡና ተመልሶ ሲያለገለግል ቆይቶ አሁን መዳረሻው በአሰልጣኝ አሸናፊ በቀለ የሚመራው ሸገር ከተማ ሆኗል።