ሲዳማ ቡና የግብ ዘቡን ውል አራዝሟል

ሲዳማ ቡና የግብ ዘቡን ውል አራዝሟል

በአሰልጣኝ ያሬድ ገመቹ የሚመሩት ሲዳማ ቡናዎች የግብ ጠባቂያቸውን ውል አራዝመዋል።

ለ2018 የውድደር ዘመን ቅድመ ዝግጅታቸውን ለመጀመር የተቃረቡት ሲዳማ ቡናዎች ወደ ዝውውሩ በመግባት አሁን የግብ ዘባቸውን መስፍን ሙዜን ለተጨማሪ ዓመት በቡድኑ ለማቆየት መስማማታቸውን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

በሀዋሳ ታዳጊ ቡድን ጅማሮውን ያደረገው ግብ ጠባቂው በከፍተኛ ሊግ ወልዲያ፣ ባቱ ከተማ እና ከሁለት ዓመት በፊት ነበር ቤንች ማጂ ቡና ባደረገው ጥሩ እንቅስቃሴ ሲዳማ ቡናን የተቀላቀለው። በሲዳማ ቡና ያለፉትን ሁለት ዓመታት በአመዛኙ ጨዋታዎች ላይ የተሳተፈው መስፍን በኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን መጫወቱም ይታወቃል። አሁን ለተጨማሪ ሁለት ዓመት በሲዳማ ቡና የሚቆይበትን ስምምነት ፈፅሟል።