ቢጫዎቹ ቡድናቸውን ማጠናከር ተያይዘውታል

ቢጫዎቹ ቡድናቸውን ማጠናከር ተያይዘውታል

በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት በቡናማዎቹ ቤት ጥሩ ቆይታ የነበረው ተጫዋች ቢጫዎቹን ለመቀላቀል ከስምምነት ደርሷል።

በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት የታንዛንያውን ያንግ አፍሪካንስ በመልቀቅ ወደ ኢትዮጵያ ቡና ተቀላቅሎ ከክለቡ ጋር ስምንት ግቦችን በማስቆጠር ጥሩ ቆይታ ያደረገው ጋናዊው የፊት መስመር ተጫዋች  ኮንኮኒ ሐፊዝ ወደ ወልዋሎ ለማምራት ተስማምቷል።

በሀገሩ ክለብ ቦልጋ ኦል ስታር እግር ኳስን ከጀመረ በኋላ ባለፉት ዓመታት በቤከም ዩናይትድ፣ በሰሜን ሳይፕረስ ክለቦች ኣልሳንካክ የሺሎቫና ባፍ ኡልኩ ዩርዱ እንዲሁም ለሊብያው ኦሎምፒክ አዛውያ እና ለታንዛንያው ያንግ አፍሪካንስ ከተጫወተ በኋላ በ2017 መጀመርያ ወደ ኢትዮጵያ መጥቶ በኢትዮጵያ ቡና ቆይታ ያደረገው አንድ ሜትር ከሰማኒያ አምስት ሴንቲ ሜትር የሚረዝመ ቁመታሙ አጥቂ በቡናማው መለያ 29 ጨዋታዎች ላይ ተሳትፎ 2209′ ደቂቃዎች ቡድኑን ያገለገለ ሲሆን በውድድር ዓመቱም በፕሪምየር ሊጉ 7፣ በኢትዮጵያ ዋንጫ ደግሞ አንድ በድምሩ 8 ግቦችን ከመረብ ጋር አዋህዷል።