ጦሩ አጥቂ አስፈርሟል

ጦሩ አጥቂ አስፈርሟል

በአሠልጣኝ ሙሉጌታ ምሕረት የሚመራው መቻል የአጥቂ መስመር ተጫዋች የግሉ አድርጓል።

በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት በተጠበቀው ልክ ተፎካካሪ መሆን ያልቻለው መቻል በክረምቱ የአሠልጣኝ ቡድኑን እንደ አዲስ ከማዋቀር ጀምሮ አዳዲስ ተጫዋቾችን ወደ ስብስቡ እያመጣ እንደሚገኝ ይታወቃል። የቅድመ ውድድር ዝግጅቱን ደብረ ዘይት ላይ እየከወነ የሚገኘው ክለቡ ተጨማሪ ተጫዋች ማስፈረሙን ሶከር ኢትዮጵያ አረጋግጣለች።

ቡድኑን የተቀላቀለው ተጫዋች ቻርለስ ሙሴጌ ነው። በጣና ካፕ ውድድር ከሞደርን ጋዳፊ ክለብ ጋር ወደ ኢትዮጵያ መጥቶ የነበረው ቻርለስ በውድድሩ በድሬዳዋዎች ዐይን ገብቶ ለድሬዳዋ ከተማ ፊርማውን ያኖረ ሲሆን ያለፉትን ሦስት ዓመታት በብርቱካናማዎቹ ቤት ካሳለፈ በኋላ ወደ ጦሩ ቤት በአንድ ዓመት ውል አምርቷል።