ባለፈው የውድድር ዓመት በሲዳማ ቡና ቆይታ የነበረው ዩጋንዳዊው ግብ ጠባቂ አዲስ ክለብ ተቀላቅሏል።
በ2017 የውድድር ዓመት ከዩጋንዳው ቡል ወደ ሲዳማ ቡና ተዘዋውሮ በውድድር ዓመቱ በ20 ጨዋታዎች ተሰልፎ 1753′ ቡድኑን ያገለገለው ዩጋንዳዊው ቶማስ ኢካራ ከሲዳማ ቡና ጋር ያለውን ውል መጠናቀቁን ተከትሎ ዳግም ወደ ሀገሩ በመመለስ ለቀድሞ ክለቡ ቡል ፌርማውን አኑሯል።
ወደ ኢትዮጵያ ከመምጣቱ በፊት በቡል፣ ፖሊስ፣ KCCA፣ ምባራራ እንዲሁም በቡሶጋ ዩናይትድ የተጫወተው ግብ ጠባቂው በሲዳማ ቡና ካደረገው የአንድ ዓመት ቆይታ በኋላ ከክለቡ የለቀቀውን ግብ ጠባቂ ጆኤል ሙታኩብዋን ለመተካት ዳግም ክለቡን ተቀላቅላል።