የ2016 የሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ኮከብ ተጫዋች ከቻምፒዮኖቹ ጋር ተለያይታ ወደ ሌላኛው የሊጉ ቡድን አምርታለች።
ከወጣቶች እና ስፖርት አካዳሚ ከተገኘች በኋላ በመቻል ፣ ሀዋሳ እና ኢትዮ ኤሌክትሪክ ቆይታ የነበራት አማካይዋ ሲሳይ ገብረዋህድ በ2016 ለኤሌክትሪክ በሰጠችው ግልጋሎት የውድድር ዓመቱ የሊጉ ኮከብ ተጫዋች ተብላ መሰየሟ ይታወሳል። ሆኖም ከአንድ ዓመት በፊት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክን ተቀላቅላ በሚጠበቀው ልክ የጨዋታ ጊዜ ያልነበራት አማካይዋ ከቻምፒዮኖቹ ጋር በመለያየት በቀድሞ አሰልጣኟ መሠረት ማኔ የሚሰለጥነውን መቻልን ተቀላቅላለች።