ከሸገር ከተማ ጋር ተስማምቶ የነበረው የመስመር አጥቂ የ2016 ሻምፒዮኖቹን ተቀላቅሏል።
በቅርቡ በአዲስ አበባ ከተማ ሕዳሴ ዋንጫ ላይ ተሳትፎ ያደረገው እና አብዛኛው የቡድን ጠንካራ ተጫዋቾችን ያጣው እንዲሁም በዝውውሩ መስኮቱ ላይ የጎላ ተሳትፎ ያላደረገው ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የመስመር አጥቂውን ፀጋዬ ብርሀኑ ለማስፈረም መስማማቱን አውቀናል።
ከወላይታ ዲቻ ተስፋ ቡድን የተገኘው ፀጋዬ ብርሀኑ በሀዲያ ሆሳዕና መጫወት የቻለ ሲሆን በዘንድሮው የውድድር ዓመት ደጋሚ ወዳደገበት የጦና ንቦች ቤት በመመለስ ማገልገሉ ሲታወስ አሁን ለቀናት ከቡድኑ ጋር አብሮ ሲሰራ ወደ ቆየበት ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለአንድ ዓመት ለማምራት መስማማቱ ታውቋል።
