አሠልጣኝ ውበቱ አባተ አዲስ ክለብ አግኝተዋል

አሠልጣኝ ውበቱ አባተ አዲስ ክለብ አግኝተዋል

ለሳምንታት ከቆዩበት የላይቤሪያው ክለብ ጋር የተለያዩት አሠልጣኝ ውበቱ አዲስ ክለብ ማግኘታቸው ይፋ ሆኗል።

የቀድሞ የኢትዮጵያ ቡና ፣ አዳማ ከተማ ፣ ሀዋሳ ከተማ ፣ ፋሲል ከነማ እና ሰበታ ከተማ በውጭ ሀገርም የሱዳኑን አልአህሊ ሸንዲ እና ለሳምንታት የላይቤሪያውን ‘Liberian International Shipping & Corporate Registry’ ‘Liscr’ ያሰለጠኑት አሠልጣኝ ውበተየ አባተ ከዚህ ቀደም ወዳሰለጠኑበት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ይመለሳሉ የሚሉ ጭምጭምታዎች ቢሰሙም ወደ ደቡብ ሱዳን ማምራታቸው ታውቋል።

አሠልጣኝ ውበቱ የደቡብ ሱዳን ሊግ ሻምፒዮን እና ሀገሪቷን በቻምፒየንስ ሊግ የወከለውን ጃሙስ የተባለውን ክለብ ለማሰልጠን የሦስት ዓመታት ውል ለመፈረም መስማማታቸውን የሀገሪቱ በርካታ የመገናኛ ብዙሃኖች እየዘገቡ ይገኛሉ።