ቢጫዎቹ የአፍሪካ መድረክ ጨዋታቸው የሚያደርጉበት ከተማ ታውቋል

ቢጫዎቹ የአፍሪካ መድረክ ጨዋታቸው የሚያደርጉበት ከተማ ታውቋል

ወልዋሎዎች ከሜዳቸው ውጭ የሚያካሂዱት ጨዋታ የሚደረግበት ሀገር ታውቋል

የኢትዮጵያ ዋንጫ አሸንፈው በታሪካቸው ለመጀመሪያ ጊዜ በካፍ ኮንፌደሬሽን ዋንጫ የሚሳተፉት እና በውድድሩ የመጀመሪያ ቅድመ ማጣሪያ ጨዋታ ከሱዳኑ አል ሂላል አል ሳህል ጋር የተደለደሉት ወልዋሎዎች ከሜዳቸው ውጭ የሚያካሂዱት ጨዋታ በሩዋንዳ መዲና ኪጋሊ እንደሚካሄድ ታውቋል።

የአል ሂላል አል ሳሕል የልዑካን ቡድን ዛሬ ረቡዕ ከሰዓት በኋላ ከፖርት ሱዳን ተነስተው በሩዋንዳ ዋና ከተማ ኪጋሊ ያረፉ ሲሆን ከወልዋሎ ጋር ላለባቸው የካፍ ኮንፌደሬሽን ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታ ቅድመ ዝግጅት ለማድረግ እና የሜዳቸውን ጨዋታ በሩዋንዳ ለማድረግ ወደ ሀገሪቱ እንዳቀኑም ታውቋል።

በቦርድ አባላቱ አብደል ዋሃብ ሐኪም ፣ ማጂድ መሐመድ አብደል ማጂድ እና በክለቡ ዳይሬክተር ያሰር ዊታ የተመራው የልኡካን ቡድኑ 25 ተጫዋቾች ይዞ ዛሬ ወደ ኪጋሊ ከተማ የገባ ሲሆን ስብስቡን ያልተቀላቀሉ ተጫዋቾች ደግሞ በቀጣይ ቀናት እንደሚቀላቀሉ ታውቋል።