ሐይቆቹ ግብ ጠባቂ ለማስፈረም ተስማሙ

ሐይቆቹ ግብ ጠባቂ ለማስፈረም ተስማሙ

ቤኒናዊ ግብ ጠባቂ ሀዋሳ ከተማን ለመቀላቀል ከስምምነት ደረሰ

በርከት ያሉ ነባር ተጫዋቾች በቡድኑ ለማቆየት ከስምምነት ደርሰው በዝውውር ቃልኪዳን ዘላለም፣ ብሩክ በየነ ፣ ሙሴ ከቤላ ፣ ቃልአብ ውብሸት እና ሬድዋን ናስርን ለማስፈረም ከስምምነት የደረሱት ሐይቆቹ አሁን ደግሞ ቤኒናዊው ግብ ጠባቂ ሴርጌ ኦባሳ ለማስፈረም ከስምምነት ደርሰዋል።

ከዚ ቀደም በካኖ ፒላርስ እና ሬሞ ስታርስ ቆይታ ያደረገው ይህ ግብ ጠባቂ በሬሞ ቆይታው በ2025/26 የውድድር ዓመት ከክለቡ ጋር ‘የNPFL ዋንጫ’ ያነሳ ሲሆን ከዛ በፊት በነበረ ዓመትም በ2024/25 በ28 በሊግ ጨዋታዎች ውስጥ በ 15 ቱ መረቡን በማስከበር የሊጉ ምርጥ ግብ ጠባቂ ክብርም መጎናፀፍ የቻለ ግብ ጠባቂ ነው።

በናይጄሪያ ፕሪምየር ሊግ ካሳየው ድንቅ ብቃት በኋላ በአሰልጣኝ ጌርኖት ሮህር የመጀመሪያ የብሔራዊ ቡድን ጥሪ የደረሰው ግብ ጠባቂው በአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ እንዲሁም በዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታዎች ሀገሩን ማገልገል ችሏል።