በአሰልጣኝ ተመስገን ዳና የሚሰለጥኑት ሀዋሳ ከተማዎች ስብስባቸውን ማጠናከር ተያይዘውታል

ቀደም ብለው ቤኒናዊው ግብ ጠባቂ ለማስፈረም ከስምምነት የደረሱት በአሰልጣኝ ተመስገን ዳና የሚመሩት ሀዋሳ ከተማዎች አሁን ደግሞ ናይጄርያዊ የመሀል ተከላካይ ለማስፈረም ከስምምነት ደርሰዋል። ቡድኑ ለመቀላቀል የተስማማው ደግሞ ቹክውብካ አንተኒ ነው።
ኢቡካ አንተኒ በሚል ቅፅል ስም የሚታወቀው ይህ
ተጫዋች የመጀመሪያ ክለቡ ከሆነው ኢፌያንዪ
በኋላ በሀገሩ ክለቦች ሬሞ ስታርስ ፣ አኳ ዩናይትድ ፣ ካኖ ፒላርስ እና ኢንጉ ሬንጀርስ መጫወት የቻለ ሲሆን ከመሀል ተከላካይነት በተጨማሪም በአማካይ ተከላካይነት መጫወት ይችላል።

