የጦና ንቦች ናይጄርያዊውን አጥቂ ለማስፈረም ተስማሙ

የጦና ንቦች ናይጄርያዊውን አጥቂ ለማስፈረም ተስማሙ

የ2024/25 የናይጄርያ ፕሪምየር ሊግ ኮከብ ግብ አስቆጣሪ ወላይታ ድቻን ለመቀላቀል ከስምምነት ደረሰ።

ከወራጅነት ስጋት አላቀው ቡድኑን በፕሪምየር ሊጉ እንዲተርፍ ያስቻሉትን የአሰልጣኝ መሳይ ተፈሪን ውል አራዝመው በዝውውር መስኮቱ የነባሮች ውል በማደስ እና አዳዲስ ተጫዋቾች በማስፈረም ላይ የቆዩት ወላይታ ድቻዎች የ2024/25 የናይጄርያ ፕሪምየር ሊግ ኮከብ ግብ አስቆጣሪ በመሆን ያጠናቀቀውን አናስ ዩሱፍን ለማስፈረም ከስምምነት ደርሰዋል።

በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት በአልጄርያው ክለብ ጄኤስ ሳውራ ቆይታ የነበረው ተጫዋቹ በሀገሩ ክለቦች ናሳራዋ እና ዊኪ ቱሪስትስ መጫወት የቻለ ሲሆን ከዚህ በተጨማሪም ከ23 ዓመት በታች እና ዋናውን የናይጄርያ ብሔራዊ ቡድን አገልግሎ በቻን አፍሪካ ዋንጫ መሳተፍ ችሏል።