በያዝነው የውድድር ዓመት እጅግ ደካማ ጉዞ እያደረገ የሚገኘው ወላይታ ድቻ ግብ ጠባቂ አስፈርሟል።
ከተከታታይ ዓመታት ተፎካካሪነት በኋላ ዘንድሮ እጅግ አስከፊ ጉዞ እያደረጉ የሚገኙት እና በ16 ጨዋታዎች 14 ነጥቦችን ብቻ በመሰብሰብ 19ኛ ደረጃ ላይ የተቀመጡት የጦን ንቦች በውድድር ዓመቱ 19 ግቦች ማስተናገዳቸውን ተከትሎ ይህንን ቀዳዳ ለመድፈን ግብ ጠባቂ አስፈርመዋል።

ቡድኑን የተቀላቀለው ሴኔጋላዊ ከሃዲም ንዳየ ሲሆን 1.94 የሚረዝመው ግብ ጠባቂ ከዚህ በፊት በሩዋንዳ ለራያን ስፖርት እንዲሁም በኬንያ ኬንያ ፖሊስ መጫወት የቻለ ሲሆን አሁን ላይ በአሰልጣኝ መሳይ ተፈሪ ለሚሰለጥኑት የጦና ንቦች ለመጫወት ፊርማውን አኑሯል።

