አራት ኢትዮጵያውያን ዳኞች አህጉራዊ ጨዋታ ይመራሉ

አራት ኢትዮጵያውያን ዳኞች አህጉራዊ ጨዋታ ይመራሉ

ኢትዮጵያውያን ዳኞች የካፍ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ጨዋታ ይመራሉ።


አራት ኢትዮጵያውያን ኢንተርናሽናል ዳኞች ቀጣይ እሁድ ጥር 24 የሞሮኮው ኦሎምፒክ ደ ሳፊ ከ ኮትዴቭዋሩ ሳን ፔድሮ የሚያካሂዱት የካፍ ኮንፌደሬሽን አራተኛ የምድብ ጨዋታ ይመራሉ። ኢንተርናሽናል ዳኛ ቴዎድሮስ ምትኩ በኤል ማሲራ ስታዲየም የሚካሄደውን ጨዋታ በዋና ዳኝነት የሚመሩት ሲሆን ኢንተርናሽናል ዳኞች ፋሲካ የኋላሸት እና ትግል ግዛው ደግሞ በረዳት ዳኝነት እንዲሁም ኢንተርናሽናል ዳኛ ማኑሄ ወልደጻዲቅ በአራተኛ ዳኝነት ተመድበዋል።

ሁለቱም ቡድኖች ከቀናት በፊት በስታደ ሎረንት ፖኩ ስታዲየም ያደረጉት ሦስተኛ የምድብ ጨዋታ በሞሮኮው ኦሎምፒክ ደ ሳፊ ሁለት ለአንድ አሸናፊነት መጠናቀቁ የሚታወስ ሲሆን በኢትዮጵያውያን ዳኞች የሚመራው የእሁዱ ጨዋታም ኦሎምፒክ ደ ሳፊ ከምድቡ መሪ ዩ ኤስ ኤም አልጀር በነጥብ ተስተካክሎ ጥሎ ማለፉን የመቀላቀል ዕድሉን ለማስፋት፤ ሳን ፔድሮ ደግሞ ነጥቡን ስድስት አድርሶ ከተጋጣሚው በነጥብ ለመስተካከል የሚፋለሙበት እንደመሆኑ ተጠባቂ ነው።