አዞዎቹ የፊት መስመር ተጫዋቹን ለማስፈረም ከስምምነት ደርሰዋል

ከአጥቂው ታምራት ኢያሱ ጋር መለያየታቸውን ተከትሎ ተተኪ የፊት መስመር ተጫዋች ለማስፈረም በእንቅስቃሴ ላይ የቆዩት አርባምንጭ ከተማዎች ፍቃዱ አለሙን ለመስፈረም ከጫፍ ደርሰዋል። በአዲስ አበባ ከተማ ፣ መቻል ቀጥሎም ለአራት የውድድር ዓመታት በዐፄዎቹ ቤት ቆይታ ካደረገ በኋላ በ2017 በኢትዮ ኤሌክትሪክ ቆይታ የነበረው ተጫዋቹ አሁን ደግሞ በሊጉ ለመትረፍ ቡድናቸውን በማጠናከር ወደ ሚግኙት አርባምንጭ ከተማዎች ለማምራት ከስምምነት ደርሷል።

