በሳውዲ ዓረብያው ክለብ እየተጫወተ የሚገኘው ጋቶች ፓኖም መቼ ብሔራዊ ቡድኑ እንደሚቀላቀል ታውቋል

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ዮሐንስ ሳሕሌ ከሳኦቶሜ እና ፕሪንሲፔ ጋር ለሚያደረጉ ሁለት የ2027 አፍሪካ ዋንጫ ቅድመ ማጣርያ ጨዋታዎች ለ23 ተጫዋቾች ጥሪ በማድረግ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሜዳ ልምምድ መጀመራቸው ይታወቃል።
ጥሪ ከተደረገላቸው ተጫዋቾች መካከልም ከዚህ ቀደም ብሔራዊ ቡድኑን በአምበልነት ያገለገለው እና ከስልሣ በላይ ጨዋታዎች በዋልያዎቹ መለያ የተጫወተው እንዲሁም በአሁኑ ወቅት በሳውዲ ዓረቢያ ሁለተኛ ሊግ በአል አረቢያ ስፖርት ክለብ የሚጫወተው ጋቶች ፓኖም ቡድኑን እንዳልተቀላቀለ መግለፃችን ይታወሳል። አሁን ባደረግነው ማጣራት መሰረት ግዙፉ አማካይ ሐሙስ መጋቢት 10 ማለዳ አዲስ አበባ እንደሚገባና ረፋዱ ላይ የብሔራዊ ቡድኑን ልምምድ እንደሚገኝ አውቀናል።

