ምዓም አናብስት የፊት መስመር ተጫዋች ለማስፈረም ተስማሙ

ምዓም አናብስት የፊት መስመር ተጫዋች ለማስፈረም ተስማሙ

ኮትዴቭዋራዊው ተጫዋች ወደ መቐለ 70 እንደርታ ለማምራት ከስምምነት ደርሷል

ቀደም ብለው ናይጄርያዊው የፊት አጥቂ አይባሚ ፕሪንስ ኦፊሬ ለማስፈረም የተስማሙት መቐለ 70 እንደርታዎች አሁን ደግሞ ኮትዴቭዋራዊው የመስመር ተጫዋች ዓብዱልለጢፍ ባምባ ለማስፈረም ከስምምነት ደርሰዋል።

በሀገሩ ክለብ ሳን ፔድሮ የእግር ኳስ ሂወቱ ጀምሮ በመቀጠልም ለሬሲንግ ክለብ አቢጃን፣ ኤሴክ ሞሞሴስ እንዲሁም በአንጎላው ክለብ ሳግራዳ፤ በደቡብ አፍሪካው ቲ ኤስ ጋላክሲ፤ በሊንያው አል ሱልፊኡም እና በጋናው አድዋና ስታርስ መጫወት የቻለው ይህ ተጫዋች አሁን ደግሞ በሀገሩ ክለብ ስታደ አቢጃን የነበረውን ቆይታ በማጠናቀቅ ወደ መቐለ 70 እንደርታ ለማምራት ከስምምነት ደርሶ ከሰዓታት በፊት አዲስ አበባ ገብቷል።